image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ለአቅመ ደካማ ለሆኑ ነዋሪዎች እና ምገባ ማዕከል ተጠቃሚ እናቶች የማዕድና የእንጀራ ምጣድ ድጋፍ አደረገ።

ህዳር 10, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሄለን መሃመድ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት አቅም ለሌላቸውና በዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖሩ በመደገፍ አብሮነታችንን በማጠናከርና በያዝነው ሰው ተኮር ተግባር እራሳችሁን የምችሉበት ድጋፍ በማድረግ በኢኮኖሚ የራሳችሁን ገቢ እንዲኖራችሁ ታስቦ የተደረገ ድጋፍ ነው በማለት ገልፀዋል። የተደረገው ድጋፍና የማዕድ ማጋራት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ከአረጋውያን ለአካል ጉዳተኞች በማድረግ አብሮነታችንን የሚያጎነብትና የሚያጠናክር ነው ያሉት ወ/ሮ ሄለን አያይዘው በተደረገው ድጋፍ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ መስጋብሩን የሚያጠናክርና እራሳቸውን የሚችሉበት ነው ሲሉ ገልፀዋል። የተሰጣቸው የእንጀራ ምጣድ በመጠቀም እራሳቸውን ወደ ስራ ማግባት እንዲችሉና ቤተሰባቸውን ከጥገኝነት እንዲያላቁ እንደሚገባ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች