image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ቢሮ ጋር በመተባበር በ2018 በጀት አመት ከነባሮቹ 1000 ነፍሰ ጡር እና አጥቢ እናቶች ፕሮግራሙን ይፋ አደረገ።

ታህሳስ 11, 2017
በክ/ከተማው ለተፈቀደው አዲስ ኮታ 260 አዲስ የተመለመሉ የአልሚ ምግብ ድጋፍ ተጠቃሚ እናቶች ፕሮግራሙን አስመልክቶ ግንዛቤ በመስጠት ፕሮግራሙን ይፋ ተደርጓል የልደታ ክፍለ ከተማ ሴ/ ህ/ማ/ጉ/ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሄለን መሀመድ ለተጠቃሚዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት በማስተላለፍ ክብርት ከንቲባችን ለህጻናት ትኩረት በመስጠት ከሚያከናዉኗቸው ተግባራት አንዱ የሆነውን ይህ ፕሮግራም በተገቢው ሁኔታ በመጠቀምና ለታለመለት አላማ በማዋል የነገ ኢትዮዽያን የዛሬዎቹ ህጻናት ላይ መስራት አለብን የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። መንግስት ልክ እነደ ፕሮጀክት ህፃናት ላይ በመስራት የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን በማስፋት በአካልም በጤናም ብቁና ንቁ ትውልድ በመፍጠር ረገድ ዘርፈ ብዙ ሚና እየተጫወተ እንደሆነ ወ/ሮ ሄለን ገልፀዋል። ከአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናት ማ/ጉ/ ቢሮ የተገኙት ወ/ሮ መንበረ በበኩላቸው ኢሲዲ በ5 አይነት እየተሰራ እንደሚገኝ እና የዛሬው የአልሚ ምግብ ተጠቃሚ እናቶች ደሞ ለታለመለት አላማ በማዋል ህፃናትን ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች