`

የዜጎች የስምምነት ሰነድ |
Citizens Charter

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ለክ/ከተማው ነዋሪዎች የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በእኩልነት፣ በግልጽነትና በፍትሃዊነት መርህ መሠረት ለመስጠት እንዲቻል የክ/ከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት በተገቢው ሁኔታ በማደራጀት ወደ ተግባር ገብቷል፡፡ በክ/ከተማዋ ካለው ነዋሪ ሕዝብ ከፍተኛው ቁጥር የሚይዙት ሴቶችና ሕፃናት በመሆናቸው፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን እንዲሁም ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አካላት ድጋፍና ክብካቤ ማድረግ አስፈልጓል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በፊት በተለያዩ ተቋማት በተበጣጠሰ፣ የተግባርና ሃላፊነት መደራረብ፣ ለአገልግሎት ተቀባዮች እሴት የማይጨምሩና ለእንግልት የሚዳርጉ በመሆናቸው እንዲሁም የሴክተሩን ልዩ ባህሪ፣ የተገልጋይ እና የባለድርሻ አካላት ፍላጎት ያማከለ ባለመሆኑ የሚጠበቅበትን ውጤት ሊያመጣ ባለመቻሉ ዳግም እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡

በመሆኑም የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላት እንደገና መቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 74/2014 ዓ.ም ለተቋሙ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት ለተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለው፣ ውጤታማና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል ይህ የዜጎች የስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡ የስምምነት ሰነዱ ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች፣ አገልግሎቶቹ የሚሰጡበትን የስራ ክፍል፣አገልግሎቱን ለማግኘት የሚፈጀው ጊዜ እንዲሁም አገልግሎቱን ለማግኘት የአገልግሎት ተጠቃሚው ማሟላት ያለበትን ቅድመ ሁኔታዎች በግልፅ አስቀምጧል፡፡ ስለዚህ ዜጎች ተገቢውን አገልግሎት ካላገኙ በየደረጃው ላሉ ኃላፊዎች ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት አግባብ በቻርተሩ ተመላክቷል፡፡ በዚህም ዜጎች ፍትሐዊ፣ ግልፅና ቀልጣፋ አገልግሎት የማግኘት መብታቸው የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡

የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ

  1. ተገልጋዮች በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተጠቃሚ ሆነውእርካታቸውን በሚያሻሽል መልኩ አገልግሎት ለመስጠት፤
  2. ይህ የስምምነት ሰነድ ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ተገልጋዮች ህግና አሰራሩን ጠብቀው ያለምንም መሸራረፍ መብታቸውን በተሟላ መልኩ እንዲያገኙ ሲሆን ይህንንም ለአመራሩ፣ ለሰራተኛውም እና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ግልጽ ለማድረግ ከዚህም ባሻገር ደግሞ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በማይወጡ አካላት ላይም ተቋሙ የገባውን የህሊና ውል መሰረት አድርጎ የተጠያቂነት አሰራርን ለማጎልበት ያለመ ነው፡፡
  3. የዜጎችን የመረጃ ማግኘት መብት ለማረጋገጥ እና
  4. ለዜጎች ግልፅ፤ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለበትና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡

የፅ/ቤቱ ተገልጋዩች

  1. ሴቶች
  2. ህፃናት
  3. በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች / አካል ጉዳተኞች፣ አረጋዊያንና ችግረኛ ቤተሰቦች/
  4. የማኅበራዊ ኑሮ ጠንቅ ተጠቂዎች /የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ ወሲብ ንግድ ተዳዳሪዎች አካልና አእምሮ የሚያደነዝዙ የአልኮልና የአደገኛ ዕጽ ተጠቃሚዎችና የሱሰ ተጠቂዎች፣የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው የህ/ብ ክፍሎች፣ ለምኖ አዳሪዎች
  5. የአፅም ይዛዋርልኝ ጠያቂዎች

የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

    የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Duties and Responsibility ይጫኑ

የተገልጋዮች መብት

  1. ምንም ልዩነት ሳይደረግበት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የመሆን፣
  2. ማንኛውም ተገልጋይ በአገልግሎቱ አሰጣጥና በአገልግሎት ሰጪው ቡድን/ሠራተኛ ላይ ያለውን አስተያየትና ቅሬታ የማቅረብ፣
  3. በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዝርዝር የማወቅና የመጠቀም፤
  4. ተገቢ የሆነ ድጋፍና እገዛ የማግኘት፤
  5. ቀልጣፋ አገልግሎት የማግኘት፤

የተገልጋዮች ግዴታዎች

  1. ሕጎችንና የአሰራር መመሪያዎችን መከተል
  2. ለሚፈልጉት አገልግሎት የተሟላና ትክክለኛ መረጃ የማቅረብ፣
  3. ተገልጋዬች አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ
    ተፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላት