Welcome to Lideta Subcity Administration!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በሰላም መጡ!       Baga Gaara Kuta Magaalaa Lideta Nagaan Dhuftan!

የልደታ ሴቶች ፣ ህጻናትና
ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት

የልደታ ሴቶች ፣ ህጻናትና
ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

የልደታ ክፍለ ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት የሴቶችን፣የህጻናት መብትና ጥበቃ፣ የአካል ጉዳተኛ እና የአረጋዊያንን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በባለቤትነት ይዞ እየሰራ ያለ ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡

ከተጠቀሱት መካከልም በጥያቄሽ ያነሳሽዉን የህጻናት መብትና ጥበቃ እንዲሁም ጉልበት ብዝበዛ በተመከለተ ሲሆን የህጻናትን ጉዳይ በተመለከተ ሃገራችን በዓለም ዓቀፍ ስምምነትና በአፍርካ ቻርተር ፈርማ የተቀበለችዉን ኃላፊነትና ግዴታን እንዲሁም በሀገራችን ህገ-መንግስት አንቀጽ 36 ላይ የህጻናትን መብት አስመልክቶ የሰፈረዉን ህገ-መንግስታዊ ሃላፊነትን ለመተግበር እየሰራች ያለች መሆኗ ይታወቃል፡፡ የህጻናት ጉዳይ የሁሉም አካላት ጉዳይ ስለሆነም የሚመለከተዉን አካል ሁሉ በማሳተፍ የሚሰራ ስራ ነዉ፡፡ ከዚህ አንጻር የህጻናትን... ተጨማሪ ያንብቡ

ወ/ሮ ሄለን ሙሐመድ , የልደታ ሴ/ህ/ማህ/ጉ/ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ዋና ዋና አገልግሎቶች

በልደታ የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች:-

በዝርዝር ይመልከቱ

የልደታ ክ/ከተማ ሴቶች ፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ ሴቶች ፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡